#ከአመታ በፊት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአካባቢ ብክለትን ለማስወገድ የወጡ ግቦች አንዳቸውም አለመሳካታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

የዓለም ብክለትን ለማስወገድና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ እ.ኤ.አ በ2010 የዓለም መሪዎች “የአይቺ የብዝሀ- ህይወት አለማዎች” የተባለ የ10 አመት እቅድ መንደፋቸው ይታወሳል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው የአካባቢ ብክለትን ለመግታት ሀገራት ካወጧቸው ሀያ እቅዶች ውስጥ አንዳቸውም ሙሉ በሙሉ አልተሳኩም ተብሏል፡፡

የተመድ ሪፖርትን ጠቅሶ ሲኤን ኤን እንደዘገበው ሀገራት ካቀዳቸው 20 ግቦች ውስጥ 6ቱ በከፊል ብቻ ተሳክተዋል፡፡

source #ኢቢኤስ  #EBS

Leave a Reply

Your email address will not be published.